Born in Addis Ababa, Shewandagn Hailu started his music career at St. Joseph high school playing English songs and grew in his career working with different bands.
He later formed his own popular band 'Afro-sound band' and released two well-liked albums. Friends and colleagues of Sheandagn who knew him since a student express Shewandagn with his strong and very charming personality.
Journalist Tsion Girma produced this documentary talking to Shewandagn's friend since high school Girum Mezmur, and his best friend and colleague Tewodros Kassahun aka. Teddy Afro, renowned music composer Abegasu Shiwota, Kamuzu Kassa and the legendary and Yared music school lecturer Feleke Hailu. The documentary titled 'Shewandagn Hailu and his professional life' also include Shewandagn's many other friends and colleagues who have been part of his professional life.
DireTube wishes you a Merry Ethiopian Christmas and invites you to watch this documentary which was released during Shewandagn's latest album, 'Sitotash', release party.(By Tsion Girma)

ሸዋንዳኝ ኃይሉ እና ሞያዊ ሕይወቱ
አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው ድምጻዊ ሸዋንዳኝ ኃይሉ፤የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርቱን በተከታተለበት ቅዱስ ዮሴፍ ትምሕርት ቤት ሙዚቃን እንግሊዘኛ ዘፈን በማቀንቀን ጀምሮ ችሎታውን በማሳደግ ከተለያዩ ባዶች ጋር ከመሥራት ታዋቂ የሙዚቃ ባንድ እስከማቋቋም ከዚያም ተወዳጅ የኾኑ ሁለት አልበሞችን ለሕዝብ እስከማበርከት ደርሷል፡፡
ሸዋንዳኝን ከተማሪነቱ ጀምሮ አሁን እስከሚገኝበት የሞያው ደረጃ የሚያውቁት ጓደኞቹ እና የሞያ አጋሮቹ አንድ ላይ ተስማምተው እጅግ ጠንካራ እና ተወዳጅ ሲሉ ይገልጹታል፡፡
ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ከትምሕርት ቤት ጀምሮ እስካሁን ወዳጁ እና የሞያ አጋሩ የኾነውን ግሩም መዝሙር፣የልብ ጓደኛውና የሞያ አጋሩን አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋሱ ክብረወርቅ ሺወታ፣ካሙዙ ካሳ፣ አንጋፋው የሙዚቃ ባለሞያና የያሬድ የሙዚቃ ትምሕርት ቤት መምሕር ፈለቀ ኀይሉን ጨምሮ ሸዋንዳኝን በሞያዊ ሕይወቱ የሚያውቁትን በርካታ ወዳጆቹንና የሞያ አጋሮቹን በማነጋገር ‹‹ሸዋንዳኝ ኃይሉ እና ሞያዊ ሕይወቱ›› የሚል ዘገባዊ ፊልም አዘጋጅታለች፡፡
ዘገባዊ ፊልሙ አርቲስቱ በቅርብ ያወጣው ‹‹ስጦታሽ›› የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ሲመረቅ በጋራ የተመረቀ ሲኾን፤የድሬትዩብ ዝግጅት ክፍል ‹‹እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!›› እያለ ይህንን ፊልም እንድትመለከቱት ይጋብዛል፡፡